የህዝብና ቤቶች ቆጠራ መራዘም አንድምታው 

​የህዝብና ቤቶች ቆጠራ መጋቢት 29 ይካሄዳል ቢባልም የጠ/ሚሩ ጽ/ቤት እንዲራዘም ማድረጉ የሚታወስ ነው። የህዝብ መፈናቀል ባለበት ሁኔታ ቆጠራው ቢካሄድ ኑሮ እሚፈጥረው ውዥንብር ቀላል ኣይሆንም ነበር ፤ በዚህም የውሳኔ ለውጥ ሁሉም አሸናፊ ሆኖ ወጥቶአል። ማንም ኣሸናፊና ተሸናፊ የለም በውሳኔው ለውጥ።  የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ለምን አንገብጋቢ “ሴንሴቲቭ”  ሆነ ? ። 1 ) የፌደራል መንግስቱ ለክልሎች እሚያደርገው አመታዊ የበጀት ድጋፍ ቀመር 60 በመቶ መሠረት እሚያደርገው የክልሉን ህዝብ ብዛትን መሰረት በማድረግ ነው።  2 ) ሌላው የምርጫ ክልል ብዛትእና ክልሉ በተወካዮች እና ፌዴሬሽን ም/ቤቶች የሚይዘው ወንበር ብዛት እሚወሰነው በክልሉ ወይም በከተማው ባለው የህዝብ ብዛት ልክ ነው።  3 ) ከዚህ በመቀጠል ደግሞ የፌዴሬሽን ም/ቤት ወንበር ብዛት እሚወሰነው አሁንም በክልሉ በህዝብ ብዛት ልክ ሲሆን የህዝብ ብዛቱን ለወንበር ቁጥር ልክ በማካፈል ነው ። ስለዚህ የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ምን ያህል #Politically Sensative አንገብጋቢ እንደሆነ መገመት ይቻላል ። ይህ ብቻም ሳይሆን  ሀይማኖታዊም ሆነ ብሄራዊ ጉዳዮች በቆጠራው ውጤት እሚወሰኑ ናቸው። 

የባርነት ምራሊቲ ምንጭ ኒቼ

የባርነት ሞራሊቲ ምንጭ
Stephen Hicks, Nietzsche and the Nazis a Personal view በሚለው መጽሃፉ በምዕራፍ 5 ካሰፈረው The origin of Slave Morality የሚለውን ንዑስ ርዕስ ፍሬ ሃሳቡን ሳይለቅ በነፃ ትርጉም የቀረበ። በመጀመሪያው ክፍል ላይ የባርነት ሞራሊቲ እሴቶች እንዴት ከአይሁዳዊው ባህላዊ እሴቶች ጋር መዋሃድ እንደጀመሩ ተመልክተናል በዚህ ክፍል ደግሞ ባህላዊ እድገቱን እና ወደ ተቀረው ዓለም እንዴት ሊስፋፋ እንደቻለ እንቃኛለን። ኒቼ እያለን ያለው ታዛዥነት፣ ትህትና፣ ይቅር ባይነት፣ እና ታጋሽነት ሞራል ሊሆኑ የቻሉት ፈጣሪ ስላዘዘው እንዳልሆነ እናስተውል ነው። በመሰረታዊነት ሞራሊቲ ከሃይማኖት ጋር የግድ የሚያቆራኘው ነገር የለምና። የነዛ ባህሪያት መልካምነት የሚመሰረተው ምድር-ተከል (down-to-earth)፣ ተመራጭ፣ እና ተግባራዊው how-do-you-survive-in-a-tough-world-of-power-strugglesን ያገናዘበ ነው። እርግጥ ነው ጊዜ ያልፋል፤ እናም ብዙ ሰዎች የባህላቸውን ሞራላዊ ህግጋቶች ከየት እንደመጡ ረስተዋል። ወይም ተካፋይነት በሌለው (passive) ሕይወታቸው ስለዚህ ጉዳይ ምንም ሳያስቡበት በዙሪያቸው ያለውን የአኗኗር ሥርዓት አሜን ብለው ተቀብለው የሚኖሩ ናቸው። እንዲያውም ከባሮቹ መካከል የበግነት ባህሪ ያላቸው እና ባሪያ መሆናቸው ምንም ግድ የማይሰጣቸው አሉ። ሌሎች ግን ባርነታቸውን ይጠሉታል። እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ኒቼ የሚነግረን ተረክ ጽልመት የሚላበሰው። በግብጾች ስር በባርነት የሆኑት የተወሰኑ አይሁዶች (በሁዋላ ላይ አለቆች) እንደ ማንኛውም ሰው የመኖር የማደግ እና የራሳቸውን ማንነት ማንፀባረቅ የሚሹ ናቸው። ነገርግን ይሄን ማድረግ አይችሉም። እንደ ባሪያ ሆኖ መኖር ዘወትር እንደተበሳጩ መኖር ነው፤ ንቁ እና ታታሪ ለሆኑት ደግሞ ብስጭቱ በዛው ልክ ይጨምራል። እንደነዚህ አይነቶቹ ባሮች ጌቶቻቸውን በሃያሉ መጥላት ይጀምራሉ። የጌቶቻቸውን ትዕዛዝ ተቀብለው የግድ የሚተገብሩ በመሆናቸው ደግሞ ራሳቸውንም መጥላት ይጀምራሉ። መስራት የማትፈልገውን እንድትሰራ አለቃህ ሲያዝህ ምንድነው የሚሰማህ? ሥራውን “ወዲያ በለው!” ብለህ እምቢ ትላለህ? ወይስ የሆድህን በሆድ ይዘህ ኮስተር ብለህ የተሰጠህን ሥራ እየጠላከውም ትሠራዋለህ? ሁሌም የታዘዝከውን ተቀብለህ የምትሰራ ከሆንክና የምትሠራውን ደግሞ ሁሌ የምትጠላው ከሆነ ነፍስህን ምን የሚያደርጋት ይመስልሃል? ጫናው እየጨመረ ይሄድና ጌታህን ብቻ ሳይሆን መጥላት የምትጀምረው፣ ደካማና ያለማንገራገር ትዕዛዝ ተቀባይ በመሆንህ ራስህንም ጭምር መጥላት ትጀምራለህ። ይሄ ነገርም በውስጥህ ለትቁዋቁዋመው የማትችለውን ስነልቦናዊ ጫና በውስጥህ እንዲፈጠር ያደርጋል። በዚህ ጊዜ ነው እንግዲህ በስነልቦናህ ውስጥ አፀያፊ ነገሮችን መከሰት የሚጀምሩት። ኒቺ ይህን ሃሳብ የሚገልፀው እንዲህ ነው ፣ “ወደ ወጪ መራገፍ የነበረበት ነገር በመታፈኑ ወደ ውስጥ ተመልሶ ሰውዬውን ያጠቃል። ጥላቻ፣ ጭካኔ፤ የማሰቃየት ደስታ ፣ የማጥቃት ደስታ ፣ የመቀየር ደስታ ፣ እና የማፍረስ ደስታ በውስጥ ይርመሰመሳሉ። በደመነፍሳቸው እነዚህን በሙሉ የተሸከሙት ሰዎች መልሰው የገዛ ራሳቸው ጠላት እንዲሆኑ ያደርጉዋቸዋል። የ ‘መጥፎ ህሊና’ ጅማሮም ይሄው ነው።” (Genealogy of Morals) መጥፎ ህሊና ከያዙት መካከል አንዱ ብትሆን ራስህን እንዴት ነው የምታፅናናው? ራስህን አሰከ መጉዳት ወደ ሚደርስ ቁጣ ወይም ንዴት አለመውረድስ እንዴት ትችላለህ? ይሄ የታፈነ ኢነርጂ፣ የራስህን ምቾት በማያጓድል መንገድ በደህና አቅጣጫ እንዲፈስ ማድረግ እንዴት ነው ሚቻልህ? ጌቶችህን በገሃድ መበቀል አትችልም እዚህ ላይ ኒቺ ስለ ቄሶች እንድናስብ ይጠይቀናል። ቄሶች ማለት እንደ የተለመዱት የበግነት ባህሪ ያላቸው የሃይማኖት ተከታዮች አይነት ሳይሆኑ፤ ጎበዞች፣ ውስጣዊ መነሳሳት ያላቸው እና ለስኬታማነት ከፍተኛ ጉጉት ያላቸው ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም በውስጣቸው የሚፈጠረውን ወደ እንስሳዊ ሃይለኛነት በሚገፋፋው ስሜት እና እኔነት-አልባና ትሑታን እንዲሆኑ በሚያስገድደው ሞራሊቲ መካከል ያለውን ውጊያ በጥልቅ ስሜት የሚገነዘቡ ናቸው። ኒቺ ቄሶችን በሚጋረፉ ቃላት ነው የሚገልጻቸው፣ “ውስጣዊ ጥንካሬ ስለሚያጥራቸው የጥላቻ ስሜት በከፋ ደረጃ እና በረቀቀ መንገድ በውስጣቸው ያድጋል። በዚህም በዓለም ታሪክ ቁንጮ የጥላቻ አራማጆች ቀሳውስት ናቸው።” ( Genealogy of Morals) የአይሁዳዊ-ክርስትና ትውፊት ላይ ያሉት ቀሳውስት አዘውትረው የሚሰብኩት ምን ሆነና? ስለ አንድ ትልቅ አዕምሮ-ወለድ ብቀላ አይደለም? በጐቻቸውን ትሑታን፣ የዋሃን፣ እና ታዛዦች እንዲሆኑ ነው የሚሰብኩዋቸው። ለማን ነው ግን ታዛዥ የሚሆኑት? በእርግጥ ለእግዚአብሔር ነው። ነገርግን እግዚአብሔር ዘወትር በዙሪያቸው የለም። ስለዚህ ለእግዚአብሔር ታዛዥ መሆን ማለት ወደ ተግባር ሲመነዘር እዚህ ምድር ላይ የእግዚአብሔር ተወካዮች ለሆኑት መታዘዝ ማለት ነው። ታዲያ ማን ይመስላችሁዋል ተወካዮቹ? ቀሳውስቱ ናቸዋ! የቄሶች ከፊል ስትራቴጂ ይህ ነው : የሃይል መሠረትህን ታዛዥ ተከታዮች በሚሆኑ ግን ደግሞ ብዙ ቁጥር ያላቸውን ሰዎች ላይ መገንባት። ጥራት ያላቸውን ሰዎች ከጎንህ ላታሰልፍ ትችላለህ፤ ሆኖም አንዳንድ ጊዜ ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ጠንካራ መሣሪያ ሊሆኑ ይችላሉ። [ዴሞክራሲን ማስታወስ ነው] ሌላኛው የስብከታቸው ክፍል ደግሞ ሀብታሞችን፣ ሃይለኞችን፣ እና በራሳቸው ላይ ፅኑ እምነት ያላቸውን የሚኮንን ነው። ገንዘባቸውን እንዲበትኑ፣ ጉልበታቸውን ለደካሞች እና ለሕሙማን አገልግሎት እንዲያውሉ፣ እና ከጠቦት ጋር አንድ ላይ ተኝቶ ለምሳ እንዳያደርጋት እንደሚቆጠበው አንበሳ እንዲሆኑ ይገደዳሉ። የዚህ ሁሉ በሀብታሞች እና በሃይለኞች ላይ ያነጣጠረው ስብከት ፍሬነገር ምንድነው? አንደኛው ዓላማ በዙሪያቸው ላሉት ደካሞች እና ድሆች ማጽናኛ ይሆናል የሚል ነው። ደካሞቹ፤ ሃብታሞች እና ሃይለኞች በምላስ ሲገረፉ ባዳመጡ ጊዜ በነሱ ላይ አድሮባቸው የነበረውን የቅናት ስሜት ይቀልላቸዋል። በሌላ በኩል ግን ሀብታሞቹ እና ሃይለኞቹ ስለ ራሳቸው እና ስለ ኑሮአቸው የጸጸትና ራስን የመጠራጠር ስሜት እንዲያድርባቸው የሚያደርጉበት ቀጥተኛ መሳሪያቸው ነው። የሞራል ስብከቶቹ በጠንካሮቹ ላይ የሚወደሩ የስነልቦና መሣሪያዎች ናቸው። ደካሞቹ የጉልበት ምሽግ ስለሌላቸው የስነልቦና መሳሪያን ይጠቀማሉ። ቀሳውስት ከጌቶች ጋር በጉልበት በፍጹም ተጋፍጠው አያውቁም። ጌቶቹ ደግሞ መሣሪያ ካልታጠቀው እና ከሚንቁት ጠላታቸው ጋር መፋለም ከክብራቸው የሚያሳንሳቸዉ አድርገው ይመለከቱታል። በምትኩ ቀሳውስቱ ሞራሊቲን ጌቶቹን የሚጋፈጡበት መሣሪያ አድርገው ይጠቀሙበታል። የዋሃንን ከፍከፍ አድርገው ጠንካሮችን ይኮንናሉ። የአይሁዳዊ-ክርስትና ስነምግባር ይላል ኒቺ ፣ “ላዕላይ ደረጃ ካለው ሰው ጋር እጅግ ገዳይ የሆነ ጦርነት ገጥሞአል። የዚህን ላዕላይ ደረጃ ላይ ያለውን ሰው አይነት መሰረታዊ የደመነፍስ ባህሪያት የተወገዙ እንዲሆኑ አድርጎአልና።” (Antichrist) አይሁዳዊ-ክርስትና የበቀል ስትራቴጂው አካል ሆኖአል ብሎ ይደመድማል ኒቼ። የስትራቴጂው ሃሳብ የዱላው ጫፍ ዘወትር የሚያርፍባቸው ደካሞችን በዚህ አስቸጋሪ ዓለም ውስጥ መኖር እንዲችሉ ማድረግ ሲሆን፤ በተጨማሪ ግን የጌቶቹን በራስ መተማመን በማዋረድ አንገታቸውን እንዲደፉ እና እንዲንበረከኩ የሚያደርግ ስነልቦናዊ ብቀላ ነው። እንደማስረጃ የተለመዱትን የአይሁዳዊ-ክርስትና ተረኮችን እንድንመለከት ያስታውሰናል ኒቼ። አሁን ያሉበት ሁኔታ እንደዛ ባይመስልም ደካሞቹ፣ ህሙማኑ፣ እና ደሃዎቹ መጨረሻ ላይ እንዴት ድልን እንደሚያጣጥሙ የሚተርከውን፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደፊት እንደምትመጣና የእግዚአብሔር ቁጣም ሀብታሞችን እና ሃይለኞችን እንደምትጎበኝ የሚተርከውን የመሳሰሉት አይነቶችን። ይህን ጉዳይ በደንብ ለመግለጽ የካቶሊኩ ፈላስፋ ቶማስ አኩዋይናስን በአስረጂነት ይጠቅሳል ኒቼ፣ “የቅዱሳን ተድላና ደስታ ይበልጥ አስደሳች ይሆንላቸው ዘንድ እና ደግሞ ለእግዚአብሔር የበዛ ምስጋና ያቀርቡ ዘንድ፤ የተረገሙት ቅጣታቸውን ሲቀበሉ ቅዱሳኑ ጠንቅቀው እንዲያዩ ተፈቅዶላቸዋል።” (Summa Theologiae) ኒቺ የእነዚህን ሁሉ ሃሳቦች ፍሬነገር ጠቅለል አድርጎ በሁለት ይከፍለዋል። ማለትም የአይሁዳዊ-ክርስትና የባርነት ሞራሊቲ ትውፊት ሁለት ስትራቴጂዎች አሉት። እነሱም: በኒቼ እይታ ለዘመናት የቆየውን ውጊያ ማን አሸናፊ እንደሆነ ምንም አጠያያቂ ጉዳይ አይደለም። ከመጀመርያዋ ቤተክርስቲያን አባቶች አንዱ የሆነው ጠርጡለስ (Turtullian) መልስ በማይሰጥበት (rhetorically) ሁኔታ እንዲህ ይጠይቃል፣ “አቴንስ ከኢየሩሳሌም ጋር ምን ህብረት አላት?” በመጀመርያዋ ቤተክርስቲያን ታሪክ እንደ ጠርጡለስ ያሉ ክርስቲያኖች ከጥንታዊቷ ግሪክ ትምህርትቤቶች ከወጡት ፈላስፎች ጋር ሲከራከሩ ፈላስፎቹ እያናናቁ ነበረ የሚከራከሩዋቸው። ጠርጡለስ “አቴንስ ከኢየሩሳሌም ጋር ምን ህብረት አላት?” ብሎ የሚመልሰው የሁለቱ ትውፊቶች ፍፁም ተቃራኒነት ለማመልከት ነው። ይህ ቅራኔ የምዕራቡን ዓለም ነፍስ በበላይነት ለመቆጣጠር ለዘመናት የቆየ ትግል ነው። ኒቺ በዚህ ይስማማና ነገሩን በተለየ ሃሳብ ይገልፀዋል። ኢየሩሳሌም የምዕራቡ ዓለም ሃይማኖታዊ ትውፊት መናህሪያ ነች፤ ሁሉም ከአይሁዳዊነት ነው ሥረ ነገራቸውን የሚመዙት። በአቴንስ ምትክ ግን የአሕዛብ ትውፊትን ከፍተኛው ጫፍ ላይ አድርሳው የነበረችውን ጥንታዊትዋን ሮማ ይጠቁመናል። ሮማ ውስጥ የግሪኮች ፍልስፍና እና አርት፣ ከሮማውያኑ የሚሊቴሪ እና የፖለቲካ ጁኒየስነት ተዳቅሎ ዓለም አይታው የማታውቀውን ታላቁ ኢምፓየር መፍጠር ችሎ ነበር። ስለዚህ በኒቺ የታሪክ ንባብ የምዕራቡን ዓለም ነፍስ ለመቆጣጠር የተደረገው ታላቁ ውጊያ በሮማ እና በይሁዳ መካከል ነው። ሮማ ነች ወይስ ይሁዳ አሸናፊዋ ለሚለው ጥያቄ ደግሞ በማስረጃነት በአሁኑ ወቅት ሮማ ላይ ሰው ሁሉ ወደ ማን እንደሚንበረከክ እንድናስተውል ይጋብዘናል። አይሁዳዊ-ክርስትና ሮማን ተረክቦአታል። በኒቼ አገላለፅ፣ “በግልፅ እንደሚታየው ሁሉም ነገር አይሁዳዊ፣ ክርስቲያናዊ፣ እና መንጋዊ ሆኖአል። ” (Genealogy of Morals) ዓለም አይታ በማታውቀው ሁኔታ ታላቅዋ የጌቶች ኢምፓየር የነበረችው ሮማ፤ መሀልዋ ላይ የባሮች አለቃ ባንዲራውን ተክሎ ለረጅም ጊዜ መሠረቱን አጽንቶባታል። ይሄ ሁሉ ትልቅ የሞራል ቀውስ ነው። ቀውስ ሊባል የቻለው የወደፊቱ የሰውልጅ ጉዞ አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ ነው። ምን አይነት ዘር ነው መሆን የምንፈልገው? በምን መንገድ ነው መጉዋዝ የምንፈልገው? የምንመርጠው የሞራሊቲ ሕግ የምንጓዝበትን መንገድ ይወሰንልናል። በብዙዎች ዘንድ ብቸኛው ሞራሊቲ ተደርጎ የሚወሰደውን አይሁዳዊ-ክርስትና፣ በኒቼ እይታ ለሰውልጅ ዕድገት አደጋ አለው። ምክንያቱም ለሰውልጅ የታላቅነት እና የዕድገት ጉዞ ምክንያት የሆኑትን ሁሉንም ባህሪያት የገዛራስ እምነትን (assertiveness)፣ ራስ-መውደድን (egoism)፣ ግለ-ነፃነትን (independence) እና አደጋ ተገፋጭነትን (risk taker) ወዘተ ስለሚኮንን ነው። ይሄ ሞራሊቲ ራሱ ደግሞ የሰውልጅ ታላቅነትን የሚያዋርዱትን ሁሉንም ባህሪያት ትንሽነትን፣ የዋህነትን፣ በመሸማቀቅ በጉልበት መንበርከክን ወዘተ ከፍከፍ ያደርጋቸዋል። “በአሁኑ ወቅት ‘ሞራሊቲ’ ተብሎ ከሚወሰደው አደገኛ ጋሬጣ በላይ በሰው ዘር የዕድገትና የለውጥ መንገድ ላይ የቆመ ምንም ነገር የለም። ” እንደው ነገሩን ፍርጥ አድርጎ ለመናገር፣ ” ግልጽ አድርጌ ላስቀምጠውና የሰውልጅ ሰለ ጭካኔው ማፈር ባልጀመረበት በነዚያ ጊዜያቶች ሂዎት ከአሁኑ የበለጠ እስደሳች ነበረች።” (Genealogy of Morals) ስለዚህ አሁን ያለው የአይሁዳዊ-ክርስትና ሞራሊቲ የበላይነት፣ ጤነኛ ያልሆነ ዕድገት ስለሆነ መወገድ ያለበት ነው። ለዚህም ከበጎ እና ክፉ ባሻገር መሄድ አለብን። We must go beyond good and evil. ተፈፀመ። የኔ መደምደሚያ ኒቼ የባርነት ሞራሊቲ(evil) አምርሮ ሲፀየፈው፣ የጌትነት ሞራሊቲን (good) ከፍ አድርጎ የሚመለከተው ይመስላል። ነገርግን ለኒቼ ሞራሊቲ ከበጎ (ጌትነት) እና ከክፉ (ባርነት) ባሻገር ነው። ሆኖም ይሄ ከበጎ እና ክፉ ባሻገር ያለውን ሞራሊቲ ስሜትን በሚኮረኩሩ (poetic) ቃላት mystical በሆነ መልኩ ይገልፀዋል እንጂ በአመክንዮ አስደግፎ የገለፀው በውል የሚታወቅ ሞራሊቲ አላቀረበም። ኒቼ ያቃተውን አይን ራንድ ግሩም አድርጋ ቀምራዋለች። ይሄን እሷ ያስገኘችውን የጌታም የሎሌም ያልሆነ ግን ደግሞ ሰብዓዊ የሆነውን ሞራሊቲ በቅርቡ በአጭሩ ለመዳሰስ እሞክራለሁ። ።

Eritrea’s gulag state is crumbling

Where’s the peace dividend? 

Issaias Afwerki made peace a year ago. His people want the dividend

| ADDIS ABABA AND ASMARA

ABIY AHMED’S arrival in Asmara on July 8th last year was as colourful as it was historic. Thousands thronged the streets of the Eritrean capital to witness the first visit by an Ethiopian leader since the two countries fought a bloody war from 1998 to 2000. Both national flags fluttered along the boulevard from the airport; women carried plates of popcorn which they threw over the crowds in celebration. Eritrea’s ageing dictator, Issaias Afwerki, beamed as he embraced his young counterpart and signed a peace deal to end two decades of enmity. “There is no border between Ethiopia and Eritrea,” Abiy declared. “Instead we have built a bridge of love.”

The promise of peace was tantalising. Telephone lines and flights between the two countries were restored. Two months later the land border opened. For the first time in years Eritreans could leave their country freely. Many thought that, with the war over, Issaias would soon enact other reforms. They particularly hoped he would end the system of indefinite conscription that the UN likens to mass enslavement—and which has helped earn Eritrea the nickname “the North Korea of Africa”.

​የብሄር ፖለቲካ አመቺ የሆነ ድልዳል # fertile ground ያገኘው ስራ ኣጥና ሱሰኛ እንዲሁም መሬት ንብረት ኣልባ እንዲሁም ራሱን በዲስፕሊን ኣንጾ ለመስራትና መኖር እሚያስችል በቂ ትምህርትን ያላገኘ ወጣት በብዛት መኖር ሲሆን ፕ/ር መረራ ” የሚበላው ያጣ ህዝብ ፤ መሪዎቹን ይበላል ” የሚለው ኣባባል አውነትነት ቢኖረውም እኔ ግን ይህ ብቻ አይመስለኝም።  የተራበ ህዝብ ሊበላ የሚችለው ግፋ ቢል በአቅራቢያው የሚያገኛቸውን ጎረቤቶቹን ነው። ሲጀመር መሪዎቹን የት ኣግኝቶአቸው ? ። መሪዎቹ ወይ ዱባይ ፤ አልያም ለንደን ወይም ቤጂንግ ናቸው። ለዝህ መፍትሄው የትምህርት ስርአቱ ይፈተሽ። ብሄሩን የተለየ መብትና ጥቅም #Privilage ማስገኛ መሳርያ ኣድርጎ መነሳት ጥቅም አይኖረውም ። ይህም ወጣቱ በራሱ ስልጣን መንገድ ዘጊና የተጫነ እቃ አስቁሞ ወሳጅ ኣድርጎታል። ይህም ኢንቨስትመንትን በተለይም የውጭ ኢንቨስትመንት እንዲቀንስ ሊያደርግ ይችላል ወይም ወደ ፌይልድ ስቴት ሊቀይራቸው ይችላል አካባቢዎቹን In some areas ; It could potentially lead to failed state status. ። 

​ቤተክርስትያን ሊሠራ ሲታሰብ ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች

ቤተ ክርስቲያን ማለት ሕንፃው፣ የክርስቲያኖች አንድነት /ጉባኤ/ እና የምዕመኑ ሰውነት ማለት ነው። ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንም የተሠራው ለሦስቱም የቤተ ክርስቲያን ትርጓሜዎች መሆኑን ማወቅ ተገቢ ነው።ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ምንጩ ወይንም መሠረቱ መጽሐፍ ቅዱስ፣ የቅዱሳን አባቶቻችን ጉባኤያት ውሳኔ /ሲኖዶስ/ እና አባቶቻችን ሊቃውንት በተለያዩ ጊዜ ያደረጓቸው ጉባኤያት ውሳኔዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሥነ ሕንፃን በአጠቃላይ በሦስት ከፍሎ ማየት ይቻላል። እነርሱም ክብ ፤ መስቀል ቅርፅ/ሰቀልማ እና ዋሻ / ፍልፍል ናቸው ። ክብ ሕንጻ አብያተክርስቲያናት በብዛት በገጠሪቷ ኢትዮጵያ የሚገኙ ሲሆን ፤ መስቀል ቅርጽ ያላቸው ደግሞ በከተማ አካባቢ ይገኛሉ። ዋሻ እና ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት በብዛት በተራራማ አካባቢዎች የሚገኙ ናቸው ። (ዝርዝሩ ወደፊት ይቀርባል) የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የጥንታዊው ክርስቲያንያዊ አምልኮ ተጠብቆ ከሚገኝባቸው የክርስትና እምነት አብያተ ክርስቲያናት አንዷ ነች። የኢትዮጲያ ታሪክ ተመራማሪዎች ይህን በአብዛኛው በጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ምክንያት እና ከሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ እራሷን ለብቻዋ እንድትኖር ያደረጉትን ታሪካዊ ክስተቶችን እንደ ምክንያትነት ይጠቀሳሉ ። በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተቀበለችውን የአምልኮ ሥርዓት ጠብቃ እንድትኖር አድርጓታል። 2. ክርስትያንያዊ የአምልኮ ቦታዎች በኢትዮጵያ የታወቀው የቤተክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊ ሩፊመስ የክርስትናን ሃይማኖት ከመጀመራቸው በፊት በኢትዮጵያ ውስጥ የፀሎት ቤት መኖሩን የሚያረጋግጥ መረጃ አቅርቦልናል። በቅዱስ ፍሬምናጦስ እና በወንድሙ ኤዴሲየስ ታሪክ እንዲህ በማለት ይነግረናል “እዚያ እየኖሩ እያለ ፍሬምናጦስ የንግሥና ዘመናትን በእጁ ይዞ ነበር፤ እግዚአብሔር ልቡን አነሳሳውና ክርስትያኖች የሆኑ የሮማ ነጋዴዎችን በጥንቃቄ በመፈተሽ የአመስጋኝነት ስሜት እንዲያሳዩ እና በሮማውያን መንገድ ለጸሎት በተዘጋጁ የተለያዩ ቦታዎች እንዲሰባሰቡ አበረታታቸው” እንደ ትውፊታዊ ምንጮች ገለጻ፤ የክርስትናን ሃይማኖት እንደ መንግስት ሃይማኖት ከተቀበለ በኃላ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኢዛና በአክሱም በጣም የሚያምር ቤተክርስትያን ገንብቷል። እሱም በሠላሳ ሁለት ዓምዶች የተደገፈ ሲሆን ምንም ቅርጾች (arches) አልነበራቸውም በጥንት ክርስቲያኖች ዘመን የነበሩ የአረማውያን ዘመን ቤተመቅደሶች ወደ አብያተ ክርስቲያናት ተለወጡ። በየሀ የሚገኘው የሳባውያን የጣዖት ቤተ መቅደስ በ5ኛው ክፍለ ዘመን ከሮማ ኢምፓየር ወደ አክሱም ከመጡት ከተሰአቱ ቅዱሳን አንዱ ወደሆኑት ወደ አባ አፍጼ ቤተክርስትያንነት እንዲቀየር ተደረገ። በቅርብ በተካሄደ የአርኪዮሎጂ ቁፋሮ በዚህ ሕንፃ ምስራቃዊ ክፍል ላይ እንደ ደወል እና መስቀል የመሳሰሉ የክርስትያኖችን ቁሳቁሶች ለማግኘት ተችሏል። በተመሳሳይም በአክሱም ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው በአባ ጰንጠሌዎን ቤተክርስቲያን ተመሳሳይ ነገር ተፈጽሟል። ይህ ቦታ በአንድ ወቅት የአረማውያን አምልኮ ማዕከል እንደነበር የሚያሳዩ የሳባውያን እና የግሪክ አማልክት በዚያ ተገኝተዋል። አባ ጰንጠሌዎን የጥንቱን ቤተመቅደስ ወደ ቤተክርስቲያን ቀይረውታል ወይምን ደግሞ በቤተመቅደሱ ፍርስራሽ ውስጥ አንድ ቤተክርስቲያን ገንብተዋል። የቀድሞው የአክሱም ቤተ መንግሥት አካባቢ በአዱሊስ እና በሃውልቲ-ሜላዞ አካባቢ የተደረጉ ቁፋሮዎች የሶሪያን ባሲሊካ የሚመስሉ ፍርስራሽ ተገኝተዋል። ይህ ምናልባት በዘጠኙ ቅዱሳን ተጽእኖ ምክንያት ሊሆን ይችላል፤ ምክንያቱም አብዛኛዎቹ የሶሪያ ዝርያ እንደሆኑ ይታመናልና። ይህንን የሚመስል የባሲሊካ ቤተ ክርስቲያን ዓይነት በደብረ ዳሞ ገዳም ውስጥ ይገኛል። እንደ ቅዱሳት ገድላት ምንጮች መሠረት፤ ቤተክርስቲያኑ የተገነባው በ 6ተኛው ክፍለ ዘመን የካሌብ ልጅ የነበረው ንጉሥ ገብረመስቀል ነው። በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ የየመን መኮንን በአብርሃ አማካይነት አንድ አስደናቂ ቤተክርስትያን በሰንዓ ተገንብተዋል። ይህች ቤተክርስቲያን በአረብ ፀሐፊዎች በጣም የተከበረች ነበረች። ይህ አቅሌስያ በመባል የሚታወቀው አል-ቃሊስ ተብሎ ይጠራ ነበር። አብርሃ ከአክሱም እና ከባዛንታይም የፈጠራ ባለሙያዎችን ያመጣ ሲሆን፤ ባሲሊካን እና የባይዛንቲን ዓይነቶችን በማጣመር አስደናቂ የተራቀቀ የኪነ-ጥበብ ችሎታ ያለው ቤተ-ክርስቲያን አዘጋጅተዋል። በመካከለኛው ዘመን ውስጥ፤ የባሲሊካው አሰራር ዘይቤ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ግን ለውጥ ተደርጓል። አስደናቂዎቹ የላሊበላ ፍልፍል አብያተ-ክርስቲያናት በዚህ ወቅት የተከናወኑ ናቸው። የቤተ መድኃኔ አለም እና የገነተ ማርያም ቤተክርስትያናት ሙሉ ለሙሉ በአዲስ ኪነጥበባዊ አይነት ያጌጡ ውጫዊ አምዶች የተገነቡ ናቸው። ውስጣዊ ክፍሎቹ ከድሮዎቹ የአክሱም ቤተክርስቲያን ጋር ብዙ ተመሳሳይ ነገሮች አሏቸው። የቤተ አማኑኤል ውጫዊ ገጽታ የአክሱማዊት ዓይነቶች የአማራጭ ወደ ዉስጥ መግባትና እና ወደ ወጭ መውጣትን (recessions and projections) ያስታውሰዋል። የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናት ከወጥ ድንጋዮች የተገነቡ ሲሆኑ የክርስትና ዓለም አስገራሚ ነገሮች ናቸው። ውስጣዊ ክፍሎቹ በጥንቃቄ ከተፈለፈሉ በኋላ፤ ሃገራዊ በሆን ጥበብ ግድግዳውና ጣርያው በሚያምር መልኩ ተቀርጿል ። እያንዳንዱ ቤተክርስቲያንም በተለየ መንገድ ተገንብቷል። በመጨረሻው የመካከለኛው ዘመን የሃይማኖት ተቋማት ከፍተኛ ግንባታ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ተደረገ። ባለ ስምንት ማዕዘናዊ ወይም ክብ ቅርጽ ያላቸው አብያተ ክርስቲያናት መገንባት መገንባትም ጀመሩ። እነዚህ ቅርጾች ተሻሽለው እየጨመሩ የመምጣታቸው ምክንያት የኢትየጵያ የኃይል ሚዛን ወደ ደቡብ በመሄድ እና በደቡብ በኩል ክብ ቅርፅ ያላቸው የመኖርያ ቤቶችን ቅርጽ አግኝተዋል። የዚህ አይነት ክብ ወይም ስምንት ማዕዘናዊ ቤተክርስቲያንም ክርስትና ዘግይቶ ወደገባበት ወደ ደቡባዊና ምዕራባዊ አካባቢዎች በብዛት መገንባቱን ሲቀጥል የመጀመሪው የባሲሊካው አይነቱ ደግሞ በሰሜን ኢትዮጵያ በብዛት መኖሩን ቀጥሎበታል።

ኤርትራና ጎረቤቶቿ

​የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር በድረ-ገፁ ባሠራጨዉ መግለጫ እንደሚለዉ ሶስቱ መንግሥታት በኤርትራና በኢትዮጵያ መካከል የተጀመረዉን የሠላም ሒደት-በተለይ፣ የአፍሪቃ ቀንድን ባጠቃላይ ለማተራመስ እያሴሩ ነዉ። መግለጫዉ «እርባና ቢስ» ያላቸዉ እርምጃዎች ካታር በመደበችዉ ገንዘብና የዘመቻ አገልግሎት የሚቀነባበሩ ናቸዉ። የባህር በር አልባ #Landlocked አገር መሆን አንዱ ጥቅም አለው ከተባለ ይኽው ከሀያላኑ ፍጥጫ ነጻ መሆን ነው። በዚህ የሀብታም ዓረብ አገራትና የሀያላኑ ሽኩቻ መድረክ ከመሆን እነ ጅቡቲና ኤርትራ ፤ ሱዳን፤ ሶማልያ አላመለጡም። በአንጻሩ ኢትዮጵያ ይህ ከመጋረጃው በስተጀርባ የቀይ ባህርን የመቆጣጠር ወይም የአረብ ባህር የማድረግ ውዝግብ ወይም ትግል አይመለከታትም ። በቅርቡ ኤርትራ የቀይ ባህርን ጠረፍ ለመቆጣጠር የሚደረግ ያለችውን «የጥፋት መልዕክተኞች»  ያለቻቸዉን ቱርክን፣ ቀጠርንና ሱዳንን አውግዛለች።   የቱርክ መንግሥት፤ በጎርጎሪያኑ 2019 መጀመሪያ ላይ ለማይታወቀዉ «የኤርትራ ሙስሊም ሊግ» ሊቀመንበር፣ የኤርትራ ዑለማ ሊግ/የኤርትራ ራቢጣ-አይ ዑለማ በሚል ሽፋን ፅሕፈት ቤት መክፈቱን ይጠቅሳል። መግለጫዉ እንደሚለዉ ከጥቂት ቀናት በፊት ካርቱም፣ ሱዳን በተደረገ ስብሰባ ላይ የተሳተፉ «ጥፋት አራማጅ» ሰዎችም በኤርትራና በኢትዮጵያ ላይ የጠብ አጫሪነት መልዕክት አስተላልፈዋል። ቀጠር የኤርትራ የቅርብ ወዳጅ፣ የኤርትራና የጅቡቲ ሸምጋይም ነበረች።የቀይ ባህርን የዓረብ ባህር ለማድረግ በሳዑዲ አረቢያ የሚመሩት የዓረብ መንግሥታት ከካታር ጋር ዉዝግብ ከገጠሙ ወዲሕ ግን ኤርትራ ካታርን ትታ ከሳዑዲ አረቢያ ጎን መቆሟን አስታዉቃለች። ቱርክ ባንፃሩ ቀጥር ዉስጥ ያላትን ጦር ሠፈር አጠናክራለች።

Sigmon Fraud

ስለ ሳይኮሎጂ ሳስብ ተሎ ወደ አእምሮየ የሚመጣልኝ ታላቁ የቬንያ ሰው ሲግመንድ ፍሮይድ ነው። ፍሮይድ በሃያኛው ክፍለ ዘመን በአእምሮ ጥናት (Mind) ላይ ተፅእኖ ፈጣሪና አነጋጋሪ ከነበሩ ምሁራን አንዱ ነው። ይህ የሳይኮአናሊሲስ ጠቢብ እሱ ከነበረበት ዘመን ቀድሞ የሄደ ወይም የተሻገረ (transcend) ነው ። ሳይኮአናሊቲክ ቴራፒ የሚባል በንግግር የሚደረግ የአእምሮ ህክምና ይዞ ብቅ ሲል ብዙዎችን አስገርሟል ። ከማስገረሙም በላይ ብዙ ተከታዮች አፍርተዋል ። አብዛኛዎቹ የሳይኮሎጂ ሙሁራን የፍሮይድን ሀሳብ ሳይጠቅሱ ወይም እንደ ማጣቀሻነት ሳይጠቀሙ ማለፍ የተለመደ አይደለም። ከሁሉም በላይ ድንቅ የተባለለት የፍሮይድ ሀሳቦች የወቅቱን የስነ ልቦና ሳይንስ ሳይቀር ተፅእኖ በመፍጠር ላይ የሚገኝ በመሆኑ ነው ። ሌሎች የስነ ልቦና ተማራማሪዎች የሆነ ጥናትና ምርምር በሚያካሂዱበት ግዜ እንኳን ሳይቀር መሰረት የሚጥሉት በፍሮይድ ፅንስ ሃሳብ ነው። ፍሮይድ በመሠረቱ ስለ ሰው ልጅ ሲገልፅ በአጭሩ እንዲህ ይላል ” የሰው ልጆች ባህሪ የሚወሰነው በ Irrational force, unconscious motive, biological and instinctual drive ነው ፤ ይህንን ደግሞ ባሉት የ Psychosexual ደረጃዎች ቀስ በቀስ ያድጋል። ዋናው የፍሮይድና ተከታዮቹ የስነልቦና ማጠንጠኛ ዘዴ “Instinct ” ነው። እዚህ ላይ ፍሮይድ አክሎም የሰው ልጅ የመጨረሻ ግብ ደስታን ማግኘት ነው ይላል ። According to Freud, all humans “strive after happiness; they want to become happy and remain so” ሲግመንድ ፍሮይድ ስለሰው ልጅ ሰብእና የተረዳበት ከታካሚዎቹ ባገኘው ተመክሮ ፣ ከራሱ የህልም ትንታኔ፣ ካነበባቸው ብዙ መፅሐፍትና ካደረገው ጥልቅ ጥናትና ምርምር ነው። የፍሮይድ በንግግር የሚደረግ የአእምሮ ህክምና ዘዴ ግብ to uncover repressed memories through free association and dream analysis ” የታመቀ ትዝታን ማከም ብለው የሚቀራረብ ትርጉም ይኖረዋል ።” the therapy works by transforming what is unconscious in to what is conscious. እዚህ ላይ ሌላው ግቡ ኢጎ እንዲጠነክር በማድረግ ከሱፐር ኢጎ ጥገኝነት ነፃ ማውጣት ነው። ሳይኮኣናሊታክ ፔራፒ ከሌሎች በንግግር የሚደረጉ የአእምሮ ህክምናዎች በተለየ መልኩ ውስብስብ ነው። ረዘም ያለ ስልጠና ይፈልጋል በስልጠናው ወቅት ሰልጣኙ የአናሊሲሱ አንዱ አካል ነው። ሳይኮኣናሊታክ ፔራፒ የሚሰለጥን ሰው ለራሱም አናላይዝ ይደረጋል። ☺